የኮ///ከተማ የወረዳ 09
ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ

ወረዳችን ከመቸዉም በላይ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል!

ስለ እኛ

ምን እየሰራን ነው

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 09 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ባለፉት 7 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከሰራቸው ሰዉ ተኮር ስራዎች በተጨማሪም ወጣቱን በኢኮኖሚ፤በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሰርተዋል እየሰራም ይገኛል፡፡ ከዚህምጋር ተያይዞ አባላችንን ብሎም ወጣቱን በእያንዳንዱ ተግባር ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ተሰርቷል እየተሰራም ይገኛል፡፡ 

የተጀመረው የልማትና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ወደ ፊት ለማስቀጠል በሚደረግ የህዝብ የተደራጀ ትግል የወረዳችን ወጣቶች ክንፍ ከአመራር እስከ አባል ተግባሩን እንደ ቁልፍ ተግባርበ መውሰድ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ለአብነት ያህል የአረንጓዴ ልማት ስራ፣ የደምልገሳ፣ የሰብአዊ አገልግሎት ስራ፣ ለሰራዊታችን ድጋፍ ድጋፍ፣ ወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ወጣቱ ተደራጅቶ እንዲሰራ የማድረግ ተግባር፣ አዳዲስ አባላትን የመመልመል ተግባር፣ ከታች እስከ ላይ ያሉትን አባላት መልሶ የማደራጀት ተግባር፣ ነባር እንዲሁም አዳዲስ አባላትን የየግል እነዲሁም የተቋም እቅድ የማሳቀድ ተግባር እና ለታቀዱት እቅዶች ጠንካራና አስተማሪ ግብረመልስ የመስጠት ተግባር፣ በታቀደው እቅድ ላይ የብልጽግና ቤተሰብና የብልጽግና ህብረት አባላትን በየ ወሩ የማወያየት ተግባር እና የሪፖርት ግምገማ የማካሄድ ተግባራት ተሰርተዋል እየተሰራም ይገኛል፡፡

ይምንሰጣችሁ አገልግሎቶች

ከዚህ በታች ያሉ አገልግሎቶችን

ሰዉ ተኮር ተግባራት

የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ተከላና እንክብካቤ፣ የአቅመ ደካማ የቤት ዕድሳት፣ የማዕድ ማጋራት፣ የትምህረት ቁሳቁስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመሳሰሉ ብጎ ተግባትን እየፈፀመ ይገኛል።

የሌማት ትሩፋት ስራዎች

እንደሚታወቀው ባለፉት አመታት የተጀመረውን የከተማ ግብርና ተግባር መነሻ በማድረግ በ2017 ዓ.ም መርሃ ግብሩን እንደወረዳችንም ተግባራዊ ለማድረግ ለወጣቶች የተጀመረውን የሌማት ስራ የጓሮ ግብርና ለማስቀጠልና በዶሮ ርባታ እንዲሳተፉ ግንዛቤ በመስጠት ወደ ተግባር የገቡ የወጣት ክንፍ አባላት ጥቂት የማይባሉ ናቸው፡፡

ስራ-እድል ፈጠራ

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከወጣቶች የስራ ልምምድ ገብትው የመጣላቸው እድል እንዲጠቀሙ የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎች ሰርተናል፡፡ ከዚህ አንፃር አጠቃላይ ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን 1150 ለሚሆኑ ወጣቶች ግንዛቤ በመስጠት አጠቃላይ በተለያዩ የስራ ዘርፎች 11 ለሚሆኑ ሼድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጎል አጠቃይ በወረዳ ደረጃ በወጣት ክንፍ በ9ወር ንቅናቄ 50 የሚጠጉ ወጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጎል ፡፡

የንቅናቄ ተግባራት

የአካባቢ ፅዳት ስራ በተመለከተ እንደሚታወቀው ባለፉት አመታት የተጀመረውን ከተማችን ውብና ፅዱ የሆነች ከተማ ለመፍጠር ባለፉት 9 ወራት በወረዳችን ለ3 ጊዜ የጽዳተ ዘመቻ ማረግ ችለናል 1 ጊዜ በክፍለ ከተማ ደረጃ ሲሆን በፕሮግራሙም 450 ወጣቶች ለማሳተፍ ተችሏል፡፡

ፎቶዎች

የመስክ ፎቶዎች

Scroll to Top