እንኳን ወደ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 በደህና መጣችሁ!
እንኳን ወደ ወረዳችን ዌብሳይት በደህና መጣችሁ እያልን………………..
ስለ እኛ
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 09 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ባለፉት 7 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከሰራቸው ሰዉ ተኮር ስራዎች በተጨማሪም ወጣቱን በኢኮኖሚ፤በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሰርተዋል እየሰራም ይገኛል፡፡ ከዚህምጋር ተያይዞ አባላችንን ብሎም ወጣቱን በእያንዳንዱ ተግባር ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ተሰርቷል እየተሰራም ይገኛል፡፡
የተጀመረው የልማትና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ወደ ፊት ለማስቀጠል በሚደረግ የህዝብ የተደራጀ ትግል የወረዳችን ወጣቶች ክንፍ ከአመራር እስከ አባል ተግባሩን እንደ ቁልፍ ተግባርበ መውሰድ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ለአብነት ያህል የአረንጓዴ ልማት ስራ፣ የደም-ልገሳ፣ የሰብአዊ አገልግሎት ስራ፣ ለሰራዊታችን ድጋፍ ድጋፍ፣ ወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ወጣቱ ተደራጅቶ እንዲሰራ የማድረግ ተግባር፣ አዳዲስ አባላትን የመመልመል ተግባር፣ ከታች እስከ ላይ ያሉትን አባላት መልሶ የማደራጀት ተግባር፣ ነባር እንዲሁም አዳዲስ አባላትን የየግል እነዲሁም የተቋም እቅድ የማሳቀድ ተግባር እና ለታቀዱት እቅዶች ጠንካራና አስተማሪ ግብረ-መልስ የመስጠት ተግባር፣ በታቀደው እቅድ ላይ የብልጽግና ቤተሰብና የብልጽግና ህብረት አባላትን በየ ወሩ የማወያየት ተግባር እና የሪፖርት ግምገማ የማካሄድ ተግባራት ተሰርተዋል እየተሰራም ይገኛል፡፡