አዳዲስ መረጃዎችና የዘርፉ ሀላፊዎች መልዕክት

ወጣት ቤቴልሄም ትዳሩ
የኮ/ቀ/ክ/ከ የወጣቶች ዘርፍ ሀላፊ መልዕክት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ክንፍ ሃላፊ ወጣት ቤተልሔም ትዳሩ የሁል ጊዜ መልዕክታቸው የሆነው በአላትን ስናከብር አቅመ ደካማ ወገኖቻችን በአሉን በደማቅ ሁኔታ እንዲያከብሩ በመደጋገፍ የአብሮነት አንዱ ለሌላው የመትረፍ እሴታችንን በማጠናከር ተቋማዊ ሃላፊነታችንን እየተወጣን መሄድ ተገቢ ነው ብለዋል።

ህዝባችንን በወጣትነት ዘመናችን በማገልገልና በመደገፍ የሚጠበቅብንን ሃላፊነት መወጣት ከወጣቶች በጉልህ የሚጠበቅ ነው የሰው ተኮር ስራዎቻችን ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ከለውጡ በኋላ እየጠናከረ የመጣ ተግባር ነው በመሆኑም ወጣቱ ተግባሩን ተቀብሎ በመስራቱ ዋናው አስተሳሰቡና ጥረቱን ነው የምናየው ብለዋል።

በተጨማሪም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ታታሪና ብርቱ በመሆናቸው ከብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጋር ተቀላቅለው እየሰሩ ያሉትም ሰው ተኮር ስራዎች, ማዕድ ማጋራት, የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት, በጎነት በሆስፒታል, በሌማት ተግባራት የመሳሰሉት ላይ በይበልጥ እንዲሰሩም መልዕክታቸውን አስተላልፏል።

Scroll to Top