አገልግሎቶቻችን
አገልግሎቶቻችን
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 09 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ከዚህ በታች በዝርዝር ያስቀመጥናቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራን እንገኛለን።
ሌማት የከተማ ግብርና ተግባር
እንደሚታወቀው ባለፉት አመታት የተጀመረውን የከተማ ግብርና ተግባር መነሻ በማድረግ በ2017 ዓ.ም መርሃ ግብሩን እንደወረዳችንም ተግባራዊ ለማድረግ ለወጣቶች የተጀመረውን የሌማት ስራ የጓሮ ግብርና ለማስቀጠልና በዶሮ ርባታ እንዲሳተፉ ግንዛቤ በመስጠት ወደ ተግባር የገቡ የወጣት ክንፍ አባላት ጥቂት የማይባሉ ናቸው፡፡
የብልፅግና ቤተሰብ ውይይት
በወረዳችን 38 የብልጽግና ቤተሰብ በ7 ህብረት ስር ያሉ ሲሆን 38ቱ የብልፅግና ቤተሰብ አሁን ባለዉ ሙሉ በሙሉ የቤተሰብ ዉይይት መጀመር እንዳለበት እና የቤተሰብ ዉይይት ሳይንጠባጠብ በቋሚነት መቀጠል እንዳለበት ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የቤተሰብ ውይይት በየቀጠናው እያደረገ ነው፡፡ በዚህም 7 የብልፅግና ህብረትና 38 የብልፅግና ቤተሰብ በቋሚነት በመወያየት ላይ ይገኛሉ።
ስራ ዕድል ፈጠራ
የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከወጣቶች የስራ ልምምድ ገብትው የመጣላቸው እድል እንዲጠቀሙ የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎች ሰርተናል፡፡ ከዚህ አንፃር አጠቃላይ ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን 1150 ለሚሆኑ ወጣቶች ግንዛቤ በመስጠት አጠቃላይ በተለያዩ የስራ ዘርፎች 11 ለሚሆኑ ሼድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጎል አጠቃይ በወረዳ ደረጃ በወጣት ክንፍ በ9ወር ንቅናቄ 50 የሚጠጉ ወጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጎል ፡፡
የአካባቢ ፅዳት ስራ
እንደሚታወቀው ባለፉት አመታት የተጀመረውን ከተማችን ውብና ፅዱ የሆነች ከተማ ለመፍጠር ባለፉት 9 ወራት በወረዳችን ለ3 ጊዜ የጽዳተ ዘመቻ ማረግ ችለናል 1 ጊዜ በክፍለ ከተማ ደረጃ ሲሆን በፕሮግራሙም 450 ወጣቶች ለማሳተፍ ተችሏል፡፡
ሰው ተኮር ስራዎች
የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ተከላና እንክብካቤ፣የአቅመ ደካማ የቤት ዕድሳት፣ የማዕድ ማጋራት ፣የትምህረት ቁሳቁስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ፣የትራፊክ አገልግሎትን ፣የደም ልገሳ መርሃ ግብር ፣ኪነ-ጥበብ ስራ ፣የከተማ ግብርና ፣ከስራ ዕድል ፈጠራ ፣የፀጥታ ስራን ፣የህዳሴ ግድብ ቦንድ ፣የአካባቢ ፅዳት ስራ ፣የወሰን ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት